የስኳር መጠን (ግሉኮስ) እንዲመጣጠን ማድረግ
የ32 ዓመቷ ፈረንሳዊት ባዮኬሚስት ጄሲ ኢንሾስፔ በብዙ ተወዳጅነት ያተረፉላት ሁለት መጻሕፍቶችን ጽፋ ለንባብ አብቅታለች። መልክቶቿን የምታስተላልፍበት ‘Glucose Goddess’  በሚለው የኢንስታግራም ስሟ የምትታወቀው ጄሲ ፤  4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ተከታዮች አሏት። ጄሲ በደም ስር ውስጥ ያለን የስኳር መጠን (ግሉኮስ) በአንድ ቦታ የረጋና የማይለዋወጥ እንዲሆን ለማድረግ መሞከር አስፈላጊ መሆኑን አበክራ ታስረዳለች። ከፍተኛ እውቅናን ያተረፈላት መጽሐፏ ‘The Glucose Revolution’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀችው ሲሆን፤ ይህም ግሉኮስን በተመለከተ ውስብስብ ሳይንሳዊ እውነታዎች ዝርዝር መረጃዎች የያዘ ነው።ርዕሱ እንደሚያመለክተው፤ መጽሐፉ ትኩረት ያደረገው “አካላችን ሁሌም የሚያምረውና የሚመኘው ሞለኪውል” ግሉኮስ ላይ ነው። ሰውነታችን ግሉኮስን በተገቢው ሁኔታ እንዲያገኝ የአመጋገብ ስርአትን ማስተካከል ይገባል ትላለች።  ስኳርነት ያላቸውን ምግቦች (ግሉኮስ)ን ከመጠን በላይ መውሰድ እንደ…
last updated on 28 Sep 05:24